Skip to main content

Posts

Featured

******እሽ እንዳልሽው ይሁን**** አንቺ ባነሳሽው ባቀረብሽው ሃሳብ እኔም እስማማለሁ ያዘዝሽኝን ሁሉ አዎን አደርጋለሁ ማፍቀርሽን ማፍቀሬን እደብቀዋለሁ ይፋ አላደርገውም እመኝኝ አንቺዬ ፍቅርሽን በውስጤ እንደ ዛፍ ተክዬ ለዓለም እሰብካለሁ አላውቃትም ብዬ እሽ እንዳልሽው ይሁን የውሸት እየኖርን የውሸት እየሳቅን ፍቅርን በልባችን እንደ ማር አጣፍጠን ዓለም ሳታውቅብን በአንድ እንኖራለን ቤትም እንሰራለን ልጅም እንወልዳለን ካገኘነው በልተን ጠግበን እናድራለን ቢከፋን ተሳስበን እንደሰታለን ውዴ እንዳልሽው ይሁን አብረን እንኖራለን ከሐይቁ ዳርቻ ውሃ እንራጫለን ከቤታችን በታች  ካለችዋ ሜዳ እንሯሯጣለን ብቻ እስከዛው ድረስ የአንቺ እና እኔን ፍቅር ማንም ሰው ሳያውቀው  ከልባችን ይኑር አደራ ጠንቀቅ በይ እንዳይሰማ ሀገር በዚች በከሃዲ በብልጭልጭ ዓለም ሞቶ እንዳይቀበር!!!!!!!!!! *************************************** *************  ህዳር 2/2009 አ-ም **************

Latest posts