****ለምን  አተይኝም****
ቀን ላይ የምትመጪ ሌሊቱ አይበቃሽም
ደግሜ ስነግርሽ ለምን አትሰምኝም
ሁሌ ማስቸገሩን ለምን አተይውም
ውዴ ባክሽ ተይኝ ስራዬን ልስራበት
በሰላሜ ልማር ላንብብ ልረዳበት
በቃ አትምጪ እንግዲህ አልፈልግም እኔ
ሳይሻል አይቀርም ብቻዬን መሆኔ
አንቺም ቢሆን ውዴ በእኔ የተነሳ አትግቢ ኩነኔ
ከእንግዲህ በኃላ ራቂ ከጎኔ
ደግመሽ እንዳትመጪ እንዳታስቸግሪኝ
የእኔዋ ፍቅረኛ ****እንቅልፌ ደህና ሁኝ!!!!****
********************************
      ********አንሙት አለሙ******
           ጥቅምት 24/2009 አ-ም 

Comments

Popular Posts