አንድ  ቀን ያልፋል !!!           
ሕይወት ጣዕሯ  በዝቶ ብትሆንም ጎስቋላ
በዳገት ቁልቁለት በደጋ በቆላ
ታግለህ ለማሸነፍ ቀበቶህ ቢላላ
ዘወትር እየለፋህ ያሰብከው ባይሞላ
ችግር ስቃይ በዝቶ መፈጠር ቢያስጠላህ  
ብትለፋ ብትደክም ቢበዛ ስቃይህ
የሚበላ ጠፍቶ ቢርብህ  ቢጠማህ
አንዱን ስታልፍ አንዱ ቢደራረብብህ
አንድ ቀን ግን ያልፋል ተስፋ አትቁረጥ አይዞህ
ድንገት ሳታስበው ይሞላል  ጎተራህ
የከበደህ ሸክም ይወርዳል ከጫንቃህ
ከኋላ ይቀራል ያኔ ያስቸገረህ
ስትወጣ ስትወርድ ከፊት አየሆነ መንገድ የዘጋብህ
ቅንጣት አትሸበር ሞላ አርገው ልብህን
በፍጹም ልቦና እመን አምላክህን
ጊዜው አልደርስ ብሎ ባይሞላ እንኳን አሁን
ጠዋት ስትነሳ ማታ ስትተኛ ፈጣሪን አመስግን
አይተወንም እርሱ ከእኛ ጋር ነው ሁሌም
ምንም ብንበድለው አምላክ መሃሪ ነው ልጆቹን አይጠላም ።።።።።።።።።።።።።።
               *********”ወልደ ጊዎርጊስ””**********  

Comments

Popular Posts