*****ንብረቴ ይመለስ*****
እማራለሁ ብዬ አደራ ላልበላ
ከግማሽ መንገድ ላይ ቆሜ ላልጉላላ
ልመልስ ውለታ ለቤተሰቦቼ
ብርድ ልብስ አንሷላ ጫማየን ገዝቼ
ስመጣ ወደዚህ ሻንጣዬን አንግቼ
አላሰብኩም ነበር እንዲህ ያለ ስቃይ
ከዚያ ሁሉ መርጦ እንደሚያርፍ በእኔ ላይ
አቤት!! በእኔ ሲሆን መከራው መብዛቱ
ያ ሁሉ እያለ ወደ እኔ መምጣቱ
ከአስራ ሁለት ሺህ ሕዝብ እኔን መለየቱ
አይገርምም ግን ጎበዝ??
ሌሊት እንደተኛሁ ለዛውም ሳናውዝ
እሳቱ ሲነሳ እኔን ሊያቃትለኝ
ያን ሁሉ ውለታ አደራ ሊያስበላኝ
የመከራ ካባ አምጥቶ ሊያላብሰኝ
ከዛ ሁሉ መርጦ እኔን ሲፈልገኝ
ግን ምን ይደረጋል------------
ዘወትር በዚያች ሰዓት መነሳት ለምጄ
ስነቃ ከእንቅልፌ ከአልጋዬ ወርጄ
የሆነ ሞቅታ ተሰምቶኝ ከላዬ
ድንገት ስመለከት በአይኔ  ቀና ብዬ
የቆምኩበት ጠፋኝ ምድር ጠበበችኝ
የማየውን ነገር ማመንም አቃተኝ
በቃ ምን ልጨብጥ ወዴት ብዬ ልሂድ???
እሳት አይኔ እያየ በላዬ ላይ ሲነድ
ሰው ልሆን መጥቼ እንደ እንጨት ስማገድ
ቆርቆሮና ጣራው እንደ ቦምብ ሲንጣጣ
እኔስ የታባቴ በየት በኩል ልውጣ!
እያልኩ በውስጤ ትንሽ ደፈር ብዬ
የተቆለፈውን የዶርማችንን በር ስይዘው  ዘልዬ
ወዲያው ተከፈተ ፈጣሪዬ ረድቶኝ
ሳነባ ሳለቅስ ስጨናነቅ አይቶኝ
ከዚያማ በኋላ-------------
ጉልበቴን አውጥቼ ያለ የሌለኝን
ከ“3”ኛ ፎቅ ወረድሁ ደረጃውን   
እየተንቀጠቀጥሁ ደርሼ ከሜዳው
ያሉትን በሙሉ ባይኔ ስቃኛቸው
አልፎ አልፎ አንዳንዶቹ ሻንጣ ተሸክመው
ምንም ልብስ ሳይለብሱ ከላይ ሳይደርቡ
ቆመው ስመለከት በእምባ እየታጠቡ
ይሄኔ ትዝ አለኝ-----------
ራሴን ብቻ እንጂ ሻንጣየን አስቤ ይዤ እንዳልወጣሁኝ
ታዲያ ምን ይሆናል-----
የእኔ መትረፍ ራሱ በጣም ያስገርማል
ንብረቴን እያሰብኩ ባለቅስ ባነባ
ዳግም ተመልሼ ከእናት ሆድ አልገባ
ሻንጣዬ እንደሞላ ራሱ አይመጣልኝ!
በቃ ቻል ማድረግ ነው የት የምደርስ ነኝ
እሱ ያመጣውን እሱ እስኪወስድልኝ
በቃ መበርታት ነው ራስን ማጽናናት
ኑሮን መቀጠል ነው በተስፋ በትዕግስት
የሚሰማ ካለም ለእኛ ተቆርቋሪ
ልቦናው የቀና ጥሩ አስተዳዳሪ
የእኛን ችግር ጭንቀት አይቶ የሚረዳ
እንደወደቅን የሚያውቅ በብርዱ ከሜዳ
ካለ ፕሬዝዳንቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ
የደረሰብኝን ሂዱ ተናገሩ
አስረዱት በጸና ዳግም እንዳይረሳው
የሻንጣየን  አመድ ይምጣ ይመልከተው
ለቤተሰቦቼም  እኔን ሚረዱበት
አቅም እንደሌላቸው ደጋግሙና አስረዱት
ይመለስ ንብረቴ ድንገት የወደመው
ራሴን ሳተርፍ ተረስቶ የቀረው
አሁንም ደግሜ እናገራለሁኝ
ችግሬን ብሶቴን ያልሰማችሁ ስሙኝ
ይሰጠኝ ብርድ ልብስ አንሷላ እና ጫማ
በብርድ እና ጠጠር ሰውነቴ አይድማ
ይሰጠኝ ይሰጠኝ ይሰጠኝ “ንጉሴ”  
ከማንም ጋ አይደለም ከአንተ ጋ ነው መልሴ!!!!!!!
>>>>>>>>>>>>>>> BY A.A<<<<<<<<<<<<<
ህዳር 1/2009 አ-ም
/በ 2009 አ.ም በ ደ/ማ/ዩ በተማሪዎች ዶርሚተሪ የእሳት ቃጠሎ ንብረታቸው ለወደመባቸው ተማሪዎች መታሰቢያ/

Comments

Popular Posts